1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፈጥሮ ሀብት ማዳን ስራ በትግራይ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 29 2012

በትግራይ በየዓመቱ የተፈጥሮ ሀብት ለመታደግ የሚደረግ ነፃ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራ ዘንድሮ ከየካቲት ወር መጀመሪያ ጀምሮ እየተካሄደ ቆይቷል፡፡ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራው የሚሳተፉ ገበሬዎች እንደሚሉት ይህ ስራቸው አካባብያቸው ከበርሃማነት እየታደ፣ የተሻለ ምርት እንዲገኝ እየረዳቸው መሆኑ ይናገራሉ፡፡

https://p.dw.com/p/3aau0
Äthiopien Wiederaufforstung in Tigray
ምስል DW/M. Hailesilassie

ነፃ የአፈርና ውኃ ጥበቃ

በትግራይ በየዓመቱ የተፈጥሮ ሀብት ለመታደግ የሚደረግ ነፃ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራ ዘንድሮ ከየካቲት ወር መጀመሪያ ጀምሮ እየተካሄደ ቆይቷል፡፡ እንደ ክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ መረጃ በዘንድሮው የተፈጥሮ ሀብት ማዳን ስራ በክልሉ የሚገኝ 1.1 ሚልዮን ህዝብ እየተሳተፈበት የነበረ ሲሆን የኮረና ቫይረስ ወረርሺኝ በፈጠረው ስጋት የአመቱ እቅዱ 50 በመቶ ከተከወነ በኋላ ለግዜው ቆሟል፡፡ 

Äthiopien Wiederaufforstung in Tigray
ምስል DW/M. Hailesilassie

በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራው የሚሳተፉ ገበሬዎች እንደሚሉት ይህ ስራቸው አካባብያቸው ከበርሃማነት እየታደ፣ የተሻለ ምርት እንዲገኝ እየረዳቸው መሆኑ ይናገራሉ፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ስራ ባለሙያዎች በበኩላቸው በክልሉ የሚከወነው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ የአፈር መሸርሸርና ለምነት በመመለስ 80 በመቶ ለሚሆነው በግብርና የሚተዳደር የክልሉ ህዝብ የላቀ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ፈጥሯል ይላሉ፡፡

ሚሊዮንኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ