የተፈናቃይ መበራከትና የርዳታው ጥረት
እሑድ፣ ኅዳር 19 2014ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አሉ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጎሳን መሠረት ባደረገ ጥቃት ምክንያት በምዕራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያ እንዲሁም በምሥራቁ የሀገሪቱ ክፍል በርካቶች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው አንዳንዶቹም በያሉበት ርዳታ ለመጠበቅ ተገድደዋል። የትግራዩ ጦርነት አድማሱን አስፍቶ ወደ አማራ እና አፋር ክልል በመዝለቁም የተፈናቃዩ ቁጥርም ሆነ የዕለት ደራሽ ርዳታ ፈላጊው መጠን በጣም ጨምሯል። መንግሥት ለእነዚህ ወገኖች ርዳታ ለማቅረብ የሚችለውን እያደረገ መሆኑን ይገልጻል። ችግሩ ያሳሰባቸው በጎ ፈቃደኞችም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ኅብረተሰቡን በማስተባበር ሲንቀሳቀሱ ይታያል። አንዳንዶች እንደውም ከውጭ ከመጠበቅ ራስን መቻል ያዋጣል በሚል ጥረቱን ያበረታታሉ። ዶቼ ቬለ በዚህ ሳምንት ያካሄደው ውይይት በሀገር ውስጥ የተፈናቃዩ መበራከት፣ ለተቸገሩት ለመድረስ የሚደረገው የመንግሥትም ሆነ የበጎ ፈቃደኞች ጥረት ምን ይመስላል? በሙሉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።
ሸዋዬ ለገሠ
ታምራት ዲንሳ