1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተጠርጣሪ ቤተሰቦች

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 14 2011

የክልሉ የሠላምና ደሕንነት ግንባታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት የኮሎኔል አለበል አማረ እና የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት የብርጌድየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ቤተሰቦች እንዳሉት እስረኞቹ ፖሊስ ጣቢያ እያሉ ሠላምታ መስጠት እንኳን አይቻልም ነበር

https://p.dw.com/p/3ODSV
Äthiopien Gerichtshof in Bahir Dar
ምስል DW/A. Mekonnen

የተጠርጣሪዎች አያያዝና የቤተሰቦቻቸዉ ቅሬታ

ባለፈዉ ሰኔ 15 በአማራ ክልል መስተዳድር ባለሥልጣናት ላይ በተፈፀመዉ ግድያ ተጠርጥረዉ የተያዙ የቀድሞ ባለስልጣናት ወሕኒ ቤት እስኪዛወሩ ድረስ ከቤተ-ሰቦቻቸዉ ጋር እንዳይገናኙ ተከልክለዉ እንደነበር የሁለቱ ተከሳሾች ቤተሰቦች አስታወቁ።የክልሉ የሠላምና ደሕንነት ግንባታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት የኮሎኔል አለበል አማረ እና የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት የብርጌድየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ቤተሰቦች እንዳሉት እስረኞቹ ፖሊስ ጣቢያ እያሉ ሠላምታ መስጠት እንኳን አይቻልም ነበር። ተጠርጣሪዎቹ ወሕኒ ቤት ከተዘወሩ በኋላ ግን ማነጋገር ችለዋል።ይሁንና የኮሎኔል አለበል ደሞዝ በመቋረጡ መቸገራቸዉን የቤተሰባቸዉ አባላት ሲናገሩ፣ የብርጌድየር ጀነራል ተፈራ ቤተሰብ ግን እስካሁን ደሞዝ እንደሚያገኝ አስታዉቀዋል።የባሕርዳሩ ዘጋቢያችን ዓለምነዉ መኮንን እንደሚለዉ ስለጉዳዩ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽንን ለማነጋገር ያደረገዉ ሙከራ አልተሳካለትም።

ዓለምነዉ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ