1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተገፋው የአውሮጳ ሕብረት ልዩ ጉባኤ

ሰኞ፣ መስከረም 18 2013

ያለፈው ሳምንት ስብሰባ የተሰረዘው የሕብረቱ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ቻርልስ ሚሸል ከቅርብ ሰዎቻቸውን አንዱ በኮቪድ 19 መያዙ በምርመራ ሲረጋገጥ ሚሼል ራሳቸውን አግልለው ማቆየት በመገደዳቸው ነው።

https://p.dw.com/p/3j7xN
EU-China-Gipfel zu Markenschutz
ምስል Reuters/Y. Herman

«በዚህ ሳምንት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል»

የአውሮጳ ሕብረት አስቸኳይ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ እና ዓርብ ሊያካሂድ አቅዶ የተስተጓጎለው ጉባኤ በዚህ ሣምንት እንደሚካሄድ ይጠበቃል። ያለፈው ሳምንት ስብሰባ የተሰረዘው የሕብረቱ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ቻርልስ ሚሸል ከቅርብ ሰዎቻቸውን አንዱ በኮቪድ 19 መያዙ በምርመራ ሲረጋገጥ ሚሼል ራሳቸውን አግልለው ማቆየት በመገደዳቸው ነው። የምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ከተደረገላቸው ተደጋጋሚ ምርመራ በኋላ ከተሐዋሲው ነፃ መሆናቸው በመረጋገጡ ሕብረቱ ወሳኝ አጀንዳዎቹ ላይ ተነጋግሮ ውሳኔ ለማሳለፍ በያዝነው ሳምንት ሐሙስ እና ዓርብ ልዩ ጉባኤውን ያካሂዳል ተብሏል። በጉዳዩ ላይ የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤን ስቱዲዮ ከመግባኤ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ገበያው ንጉሤን

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ