1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተከለሰው መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ማዕቀፍ ይፋ ሆነ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 2 2012

የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለአምስት አመታት ተግባራዊ የሚደረግ የኢትዮጵያ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ማዕቀፍ ዛሬ ይፋ አድርጓል። ሚኒስቴሩ ለአንድ አመት ሲካሄድ የቆየውን የክለሳ ጥናት መሰረት አድርጎ የጤና አገልግሎት ማዕቀፉን ማሻሻሉን ገልጿል። አዲሱ ማዕቀፍ ተመጣጣኝና ጥራቱ የተጠበቀ የጤና አገልግሎትን የመዘርጋት ዓላማ ያነገበ ነው።

https://p.dw.com/p/3Stdr
Dr Amir Aman Gesundheitsminister Äthiopien
ምስል DW/Getachew Tedla HG

የተከለሰው የኢትዮጵያ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ማዕቀፍ ይፋ ተደረገ

የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለአምስት አመታት ተግባራዊ የሚደረግ ለአንድ አመት የከለሰውን የመሰረታዊ የጤና አገልግሎት ፓኬጅ ዛሬ አስተዋውቋል። የኢትዮጵያ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት አቅርቦት መከላከልን መሰረት ያደረገውን የጤና ፖሊሲ በማሳካት ረገድ በተገልጋዮች ዘንድ ለቅሬታ የተጋለጠ ነው። 

ክለሳው ተመጣጣኝና ጥራቱ የተጠበቀ የጤና አገልግሎትን በመዘርጋት በሃገሪቱ የበሽታን ጫና የመቀነስ፤ የጤና ዘርፉን በማሻሻል፣ መሰረተ ልማቶችን በመዘርጋት ህዝቡን ከበሽታ የመጠበቅ፤ የጤና አገልግሎት ስርአቱን ውጤታማነት የማሻሻል እና በዘርፉ ላይ ህዝቡ ተሳትፎው እንዲያድግ እና በውሳኔ አሰጣጡ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን የማስቻል አላማዎች ያሉት ነው።

ሰለሞን ሙጬ
ተስፋለም ወልደየስ 
አዜብ ታደሰ