1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ወቀሳ

ዓርብ፣ ነሐሴ 17 2011

የ57 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች ዛሬ በጋራ በጠሩት ጋዜጣዊ ጉባኤ እንዳሉት መንግሥትና ገዢዉ ፓርቲ የሚከተሉትን መርሕ «አግላይ» እና «ገፊ» በማለት ነቅፈዉታል።

https://p.dw.com/p/3OOOm
Äthiopien Ablehnung Wahlentwurf
ምስል DW/Y. Geberegziabeher

ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫዉን ረቂቅ ሕግ ተቃወሙ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ ያስረቀቀዉን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በድጋሚ ተቃወሙት።የ57 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች ዛሬ በጋራ በጠሩት ጋዜጣዊ ጉባኤ እንዳሉት መንግሥትና ገዢዉ ፓርቲ የሚከተሉትን መርሕ «አግላይ» እና «ገፊ» በማለት ነቅፈዉታል። የምርጫና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ረቂቅ ሕግ 48 አንቀፆች እንዲሻሻሉ ላቀረቡት ጥያቄ እስካሁን ተገቢ መልስ እንዳላገኙም የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ተወካዮች አስታዉቀዋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን ጉዳይ አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ግን ረቂቁ «የተወሰነ» ያሉት ማሻሻያ ተደርጎበታል ባይናቸዉ። ከተቃዋሚ ፓርቲዎቹ አብዛኞቹ ለመጪዉ ዓመት የተያዘዉ የምርጫ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቀዋልም።

ዮሕንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ