የተራዘመው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት
ዓርብ፣ ሐምሌ 16 2013ማስታወቂያ
ከሳምንታት ወዲህ እንደ አዲስ በማገርሸት ሌላ ምዕራፍ የያዘው የትግራይ ክልል ጦርነት እልባት አልባ የሆነው በውጭ ሃገራት ጣልቃ ገቢነት ነው ሲሉ ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ገለጹ። የትግራዩ ጦርነት ኢትዮጵያ በቃጣናው ላይ ፍላጎት ካላቸው ከውጭ ኃይላት ጋር የምታደርግ የውክልና ጦርነት ነው ያሉት ባለሙያው፤ ተራዝሞ ለወራት የቆየው ወደ ዲፕሎማሲ ጦርነት በመቀየሩ ነውም ብለዋል። አሁን ላይ በሁለቱም ወገኖች በኩል ተጨማሪ ኃይል እያሰለፈ የሚገኘው ይኽ ጦርነት የተሻለ እልባት የታጣለትን አስገዳጅ በመሆኑ እንደሆነም አስተያየታቸውን አክለዋል።
ስዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ