የተመድ የሰብዓዊና የአስቸኳይ ዕርዳታ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ጉብኝት
ረቡዕ፣ ሐምሌ 28 2013ማስታወቂያ
በትግራይ ከ5 ሚሊየን የሚበልጥ ህዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የተመድ አስታወቀ።ሰሞኑን በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የተመድ የሰብዓዊና የአስቸኳይ ዕርዳታ አስተባባሪ በእንግሊዘኛ ምህጻሩ ኦቻ ሃላፊ ማርቲን ግሪፊትዝ በትግራይ በጎበኙዋቸው አከባቢዎች የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ መፈጠሩን ተናግረዋል።ትናንት የስድስት ቀናት ጉብኝታቸውን አጠናቀው የተመለሱት ግሪፊትዝ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር አደረግን ባሉት ፍሬያማ ውይይት የእርዳታ ቁሳቁሶቹን ለተረጂዎች የማድረሱ ስራ እንዲፈጥን መስማማታቸውም ተነግሯል።ስዩም ጌቱ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ