የተመድ የረድኤት ሠራተኞችና የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም
ረቡዕ፣ ኅዳር 30 2013ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የረድኤት ሠራተኞች፣በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ መንግሥት ከፈቀደላቸው ስፍራ ውጭ ፣ኬላ ጥሰው በማለፍ ጭምር ለመግባት ባደረጉት ሙከራ ተኩስ ተከፍቶባቸው መያዛቸውን መንግሥት አስታውቋል።ሠራተኖቹ በቁጥጥር ስር የዋሉትና ጥይት የተተኮሰባቸው ሁለት የተከለከሉ ኬላዎችን አልፈው ወደ ሶስተኛዉ በመሄዳቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ድኤታና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ትናንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል ።እንዲህ ያለው ሙከራ በድርጅቱ እውቅና የተፈፀመ እንደማይሆን ግምታቸውን ለዶቼቬለ የገለፁ አንድ የሕግ ባለሙያ ሠራተኛቹ በተለይ ዋነኛ የሕወሓት ተፈላጊ አመራሮች ባሉበት አካባቢ ይህንን አድርገው ከሆነ የሀገር ሉአላዊነትን የሚጋፋ እና አደገኛ አካሄድ ነው ብለዋል።ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ