የቬንዝዌላዉ ተቃዉሞ ሰብዓዊ ርዳታ እንዲፈቀድ ይጠይቃል
ማክሰኞ፣ የካቲት 5 2011ራሳቸዉን የቬንዝዌላ ፕሬዚደንት ሲሉ የሰየሙት ዩአን ጉአይዶ ለ «DW» በሰጡት ቃለ- ምልልስ ፕሬዚደንት ማዱሮ የሃገሪቱን ሕዝብ ፍላጎት ማስቀደም ይኖርባቸዋል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። የቬንዝዌላ መንግሥት ተቃዋሚዎች በሃገሪቱ ዛሬ ይደረጋል ተብሎ ለታቀደዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ዝግጅት መድሐኒትና ምግብ እንዲሁም ፤ አንዳንድ የጽዳት መጠበቅያ ቁሳቁሶችን ወደ ሃገሪቱ ለማስገባት ጠይቆ የነበረ ሲሆን ቁሳቁሱ እንዳይገባ የቬንዝዌላ ወታደሮች ኮሎምቢያ ድንበር ላይ አግደዉታል።
« ሁሌም ቢሆን የጦር ኃይሉ ርምጃ ሊያስከትለዉ በሚችለዉን ጉዳይ ላይ እናስጠነቅቃለን። የጦር ሃይሉ የሰብዓዊ ቁሳቁሱን ወደ ሃገር እንዲገባ ይፈቅዳል የሚል ግልጽ እምነት ነበረን። ይሁንና ምግብና የሕክምና ቁሳቁሶች ወደ ሃገር እንዳይገባ አግዶአል። ይህ በሰብዓዊነት ላይ ሊፈፀም የተቃጣ የመብት ጥሰት ነዉ። በቬንዝዌላ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ በመድሃኒት እና በምግብ እጥረት ሲሞቱ በሃገሪቱ ድምፅ አልባ ወይም በድብቅ እየተፈፀመ ያለ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። መንግሥት ሕዝቡ እንዲኖር ራሱን እንዲጠብቅ ፈቃድ አልሰጠዉም። መንግሥት ሕይወታቸዉን ለሚያጡት ሁሉ ተጠያቂ ነዉ። እንደምሳሌ ለመጥቀስ ልዩ የመንግሥት ኃይላት በሳምንቱዉስጥ በተደረገ ተቃዉሞ ከ 70 ሰዎች በላይ ገድለዋል። ቀጥተኛባልሆነ ግድያ ደግሞ፤ በሃገሪቱ ለሚታየዉ የመድሃኒትና የምግብ እጥረት ምንም አይነት መፍትሄ ለማምጣት አይፈልግም» የቬኑዜዌላ መንግሥት መድሐኒትና የሕክምና ቁሳቁስ እንዳይገባ ማገዱን በመቃወም ባለፈዉ እሁድ በአስራዎች የሚቆጠሩ የሕክምና ዶክተሮች አደባባይ ወጥተዉ ነበር።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ