1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብር ኖት ቅያሪ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የፈጠረው ስጋት

ቅዳሜ፣ መስከረም 9 2013

መንግስት የብር ኖቶችን ቅያሪን ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ በህገወጥ መንገድ ተከማችተዋል ወይም  ይንቀሳቀሳሉ በተባሉ የገንዘብ ዝውወሮች ላይ  ጥብቅ  ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል። እርምጃው በተለይ በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢ ከፍ ያለ ገንዘብ ይዞ በመንቀሳቀስ የንግድ ስራውን የማከናወን  ልምምድ ባለው ማህበረሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/3ijEO
Äthiopien Sicherheitsforum
ምስል Messay Teklu/DW

የምስራቅ ኮማንድ ፖስት እየወሰደ ያለው ጥብቅ እርምጃ

መንግስት የብር ኖቶችን ቅያሪን ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ በህገወጥ መንገድ ተከማችተዋል ወይም  ይንቀሳቀሳሉ በተባሉ የገንዘብ ዝውወሮች ላይ  ጥብቅ  ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል። እርምጃው በተለይ በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢ ከፍ ያለ ገንዘብ ይዞ በመንቀሳቀስ የንግድ ስራውን የማከናወን  ልምምድ ባለው ማህበረሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ ተነግሯል። ነገር ግን የፀጥታ ኃይሉ በህጋዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው የከተማም ሆነ የገጠር ህብረተሰብ ስጋት ሊገባው አይገባም ብሏል፡፡

መከላከያን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ምዕራብ እና ምስራቅ ሀርረጌ ዞኖች ፣ የሶማሌ ፣ ሀረሪ እና የድሬደዋ አስተዳደር የፀጥታ አካላት መካከል በተካሄደ በተካሄደ የጋራ መድረክ የምስራቅ ሀርረጌ ዞን ፀጥታ ኃላፊ አቶ አህመድ  አብዛኛው በጫት እና ሌሎች ንግድ ዘርፎች ላይ የተሰማራው ህብረተሰብ በመቶሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ በእጁ ይዞ መንቀሳቀሱ በኬላ ቁጥጥር ላይ ዕየታየ ያለ ችግር ነው ፡፡የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮምሽን ረዳት ኮምሽነር አህመድ መሀመድ በበኩላቸው በሀገር ውስጥም ሆነ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሚከናወኑ የንግድ እንቅስቃሴዎች ከመመመርያ በላይ የሆነ ገንዘብ ይንቀሳቀሳል ብለዋል፡፡

Äthiopien Sicherheitsforum
ምስል Messay Teklu/DW

በውይይት መድረኩ የመከላከያ ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ዘውዱ በላይ “ትክክለኛ የሆነው የአርሶ አደር አርብቶ ፣ አደር እና ነጋዴ ጥሪት አጀንዳ አለመሆኑን” ጠቅሰው ህብረተሰቡ በዚህ ስጋት እንዳይገባው ብለዋል ፡፡ግሽበትን ለመከላከል እና የፀረ ሽብር እንቅስቃሴን አደብ የማስገዛት ዓላማ በመያዝ መንግስት ያስቀመጠው የገንዘብ ለውጥ ዕቅድ አለመሳካት አርሶ አደሩንም ሆነ የከተማውን ነዋሪ የሚጎዳ ነው ያሉት ሜጀር ጀነራል ዘውዱ ጉዳዩ ከህዝብ ጎን የመቆም እና ያለመቆም ሀገርን የማዳን እና ያለማዳን ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡በሚያደናቅፉ ሰዎች ላይም እርምጃ እንደሚወሰድ በመጠቆም፡፡በውይይት መድረኩ እንደተገለፀው በምስራቅ ተጎራባች አካባቢዎቹ ይኖራል ተብሎ የሚታሰበውን ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ለመቆጣጠር በርካታ ነባር እና አዲስ የመቆጣጠርያ ኬላዎች መመስረታቸው ታውቋል፡፡

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ