1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያ ዉጥንቅጥ

ረቡዕ፣ ጥር 8 2011

ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ የሚመሩት መንግስት ሐገሪቱ ከአዉሮጳ ሕብረት አባልነት ሥለምትወጣበት ሒደት ከሕብረቱ ጋር ያደረገዉን ሥምምነት የብሪታንያ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባላት ትናንት 202 ለ4032 በሆነ አብላጫ ድምፅ ዉቅድቅ አድርገዉታል።

https://p.dw.com/p/3Bftg
Großbritannien London - Theresa May zu Parlamentsabstimmung
ምስል Reuters

Brexit - MP3-Stereo

የዘመናዊዉን ዓለም ፖለቲካዊ ባሕል ቀረፅን የሚሉት ብሪታንያዉያን የራሳቸዉን ፖለቲካ ቅጥ ማሳያዝ አቅቷቸዉ እየተወዛገቡ ነዉ።ብሪታንያ ከአዉሮጳ ሕብረት አባልነት እንድትወጣ ሕዝባቸዉን አስፈራርተዉም፤ አባብለዉም፣አግባብተዉም ያስወስኑት የብሪታንያ ወግ አጥባቂ ፖለቲከኞች ሕዝባቸዉ ከወሰነ ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በኋላም ዉሳኔዉን ገቢር ማድረግ አልቻሉም፣አልፈለጉም ወይም አላወቁበትም።ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ የሚመሩት መንግስት ሐገሪቱ ከአዉሮጳ ሕብረት አባልነት ሥለምትወጣበት ሒደት ከሕብረቱ ጋር ያደረገዉን ሥምምነት የብሪታንያ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባላት ትናንት 202 ለ4032 በሆነ አብላጫ ድምፅ ዉቅድቅ አድርገዉታል።አንድ የብሪታንያ መንግስት ለሐገሪቱ ምክር ቤት ያቀረበዉ መርሕ ወይም ረቂቅ ደንብ በትናንቱ ዓይነት የድምፅ ልዩነት ዉድቅ ሲሆን ከመቶ ዓመት ወዲሕ በሐገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያዉ ነዉ።ከምክር ቤት አባላት ከፍተኛ ተቃዉሞ የገጠማቸዉ ጠቅላይ ሚንስር ቴሬሳ ሜይ ከዚሕ ቀደም ምክር ቤቱ የሰጠዉን የመታመኛ ድምፅ ለጥቂት አምልጠዋል።ዛሬ ደግሞ የሠራተኛ ወይም ሌበር ፓርቲ ባቀረበዉ ጥያቄ መሠረት ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚንስትሯ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የመታመኛ ድምፅ ይሰጣል።ከትናንቱ ዉሳኔ በኋላ የአዉሮጳ ሕብረትና የብሪታንያን ፖለቲካዊ ቀዉስ እንዲያስረዱን ገበያዉ ንጉሴ ከብራስልስ፣ሐና ደምሴ ከለንደን ጋብዘናል።

ሐና ደምሴ

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋለም ወልደየስ