የብሬግዚት ውል ዳግም ውድቅ ተደረገ
ረቡዕ፣ መጋቢት 4 2011ማስታወቂያ
የብሪታንያ ፓርላማ ብሪታንያ ከ16 ቀናት በኋላ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ያለ ስምምነት መውጣት አለመውጣቷ ላይ ዛሬ ማምሻውን ድምጽ ይሰጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ፓርላማው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ከአውሮጳ ህብረት ጋር የተስማሙበትን ሀገራቸው ከህብረቱ የምትወጣበትን ውል ለሁለተኛ ጊዜ ትንናት ማታ በሰጠው ድምጽ ውድቅ አድርጎታል። ፓርላማው በተለይ ብሪታንያ ከህብረቱ አባልነት ከለቀቀች በኋላ በሰሜን አየርላንድ እና በአየርላንድ መካከል ያለው ድንበር ክፍት ሆኖ እንዲቆይ የሚጠይቀውን የውሉን ክፍል ነው የተቃወመው። የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ተጨማሪ ዘገባ አዘጋጅቷል።
ገበያው ንጉሤ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ