1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሔር ብሔረሰብ ቀን ሲታሰብ

ዓርብ፣ ኅዳር 25 2013

ኢትዮጵያ በመጣችበት ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ገደማ የብሔረሰቦች መብቶችን በማሻሻል በኩል ይበል የሚል ውጤት ብታስመዘግብም፤ ሂደቱ በሃገራዊ አንድነቱ ላይ ፈተናን ከመደቀኑ አልፎ በየአከባቢው ለሚነሱ የብሔር ግጭቶች ግን መፍትሄ ሊሰጥ እንዳልቻለ ይነገራል፡፡

https://p.dw.com/p/3mEoy
Nationalfeiertag in Äthiopien
ምስል DW/Y. Geberegziabeher

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሲከበር እንዴታ?

በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች በትናንትናው ዕለት የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለ15ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል፡፡ኢትዮጵያ በመጣችበት ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ገደማ የብሔረሰቦች መብቶችን በማሻሻል በኩል ይበል የሚል ውጤት ብታስመዘግብም፤ ሂደቱ በሃገራዊ አንድነቱ ላይ ፈተናን ከመደቀኑ አልፎ በየአከባቢው ለሚነሱ የብሔር ግጭቶች ግን መፍትሄ ሊሰጥ እንዳልቻለ ይነገራል፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ሰብና ብዝሃነት አጥኚ የሆኑት ዶ/ር ኬሬዲን ተዘራ ለዶይቼ ቬለ አንዳሉት በኢትዮጵያ በብሔረሰብ ላይ የተዋቀረው ፌዴራላዊ ስርዓት ዋነኛ ተግዳሮቱ የብሔር ማንነቱን ከአገራዊ ማንነቱ ጋር እኩል ሚዛን አስጠብቆ አለመጓዙ ነው ይላሉ፡፡

የአዲስ አበባ ወሊካችን ስዩም ጌቱ አነጋግሯቸዋል።

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ