1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉይይት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 16 2011

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፖርቲዎች ወደ ጥምረት እና ቅንጅት ውስጥ በመግባት ተወዳዳሪ መሆን ካልቻሉ ለፖለቲካ ምህዳሩ መጥበብ ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገለጸ።  የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይህንን አስመልክቶ ባዘጋጀው ውይይት ላይ ፖርቲዎች ጠንካራና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በትብብርም፤ በውድድርም ሊሰሩ ይገባል ተብሏል።

https://p.dw.com/p/3McwD
EPRDF gewinnt Wahlen in Äthiopien 2015 Merga Bekena
ምስል picture alliance/AA/M. Wondimu Hailu

ፖርቲዎች ጠንካራና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በትብብርም፤ በውድድርም ሊሰሩ ይገባል

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፖርቲዎች ወደ ጥምረት እና ቅንጅት ውስጥ በመግባት ተወዳዳሪ መሆን ካልቻሉ ለፖለቲካ ምህዳሩ መጥበብ ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገለጸ።  የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይህንን አስመልክቶ ባዘጋጀው ውይይት ላይ ፖርቲዎች ጠንካራና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በትብብርም፤ በውድድርም ሊሰሩ ይገባል ተብሏል። ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ አሁን ሃገሪቱ ጭንቅ ውስጥ ባለችበት እና ፖርቲዎች በየትኛውም ቦታ በነጻነት ተንቀሳቅሰው መስራት በማይችሉበት ነባራዊ ሁኔታ ስለ ፖርቲዎች ቅንጅትና ጥምረት ውይይት ብሎ መምጣቱ ወቅቱን ያልጠበቀ እና ተገቢ ያልሆነ ነው ብለውታል። የውይይት ጽሑፍ ያቀረቡት የሥነ- አዕምሮ ባለሞያው ዶክተር ምህረት ደበበ ፓርቲዎች ከእርስ በእርስ መጠላላፍ እና ሴራ ለመውጣት በውህደት መጠናከራቸው እንደሚበጅ ገልፀዉ ያ ማለት ግን ውድድርን መዘንጋት አለባቸው ማለት እንዳልሆነ አመልክተዋል።


ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ
ተስፋለም ወልደየስ