1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤንሻንጉል ብልጽግና ፓርቲ ወቀሳ 

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 7 2013

ሰሞኑን የአማራ ክልላዊ መንግሥት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሀን የራሳችንን እርምጃዎች እንወስዳለን የሚሉ ዛቻና ማስፈራሪዎች ተገቢ አይደሉም ሲል የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ወቀሰ።የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ፣ ችግሮቹ በዛቻና በማስፈራሪያ ሳይሆን በመነጋገርና በመቀራረብ ሊፈቱ ይገባል ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3mnnP
Assosa Town Äthiopien
ምስል DW/N. Dessalegn

የቤንሻንጉል ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወቀሳ 

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት የጋራ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ሰሞኑን የአማራ ክልላዊ መንግሥት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሀን የራሳችንን እርምጃዎች እንወስዳለን የሚሉ ዛቻና ማስፈራሪዎች ተገቢ አይደሉም ሲል የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ወቀሰ።የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ፣ ችግሮቹ በዛቻና በማስፈራሪያ ሳይሆን በመነጋገርና በመቀራረብ ሊፈቱ ይገባል ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይል ድጋፍ ካስፈለገም በሁለቱ ክልሎች ፍላጎትና በፌደራል መንግሥት ፈቃድ በመነጋገር ሊሆን እንደሚገባም ሃላፊው አሳስበዋል።የአሶሳው ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ ተጨማሪ ዘገባ አዘጋጅቷል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ