1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤኒሻንጉል ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸዉ እየተመለሱ ነዉ ተባለ 

ረቡዕ፣ ሐምሌ 29 2012

ከቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል እና አማራ  ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ከዚህ በፊት በታዩ ጥቃቶች ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ሙሉ በመሉ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  የአደጋ ስጋት  ስራ አመራር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ ከሁሉም በላይ ያለምንም ስጋት መንቀሳቀስ እንዲቻል የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ ያስፈልጋል ተብሎአል።

https://p.dw.com/p/3gRtS
Äthiopien Gedeo Zone - Umgesiedelte Menschen kehren in Ihr Dorf zurück
ምስል DW/S. Wegayehu

ከሁሉም በላይ ያለምንም ስጋት መንቀሳቀስ እድንችል የአካባቢውን ሰላም ይጠበቅልን


ከቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል እና አማራ  ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ከዚህ በፊት በታዩ ጥቃቶች ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ሙሉ በመሉ ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  የአደጋ ስጋት  ስራ አመራር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ 17ሺ  8 መቶ  81 የሚሆኑ ዜጎች በዘንድሮ ዓመት ወደ ቀድሞ ቀያቸው መመለሳቸውን  የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ተሲሳ ተናግረዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደግሞ በጉባ ወረዳ በተፈጠረው ግጭትና በስጋት ምክንያት  አንድ ሺ አንድ ሰዎች (1001) በትምህርት ቤት እና በሌሎችም ስፋራዎች ተጠልሎ እንደሚገኙም አስረድተዋል፡፡ የተፈናቀሉ ዜጎችን ዝርዝር  ጽ/ቤታቸው መረጃ እንዳለውና ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ  ጠቁመዋል፡፡ ከተፈናቀሉት መካከል በጉባ ወረዳ ያረንጃ ከተባለ ቀበሌ 200 መቶ የሚሆኑ ሰዎች በቅርብ ይመለሳሉ ብለዋል፡፡ ያነጋርናቸው ተመላሾ በበኩላቸው በተወሰኑ አካባቢዎች አርሶ አደሩ የእርሻ ስራውን እያከናወኑ መሆኑን የገለጹንል ሲሆን የሚሰጡ ድጋፎች ግን በቂ አይደሉም ብለዋል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ድጋፍ የሚባል አደረሰንም ይላሉ፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  በተፈጥሮ አደጋ ተጎጂዎች እና ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት  በተከሰተው ግጭት  ተረጂ የሆኑ 159ሺ የሚደርሱ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚገኙ  የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት አመልክቷል፡፡  ከነዚህ መከካል ከ17ሺ በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ከቤኒሻንል ጉሙዝ እና አማራ ክልል አዋሳኝ ከሆኑት አካባቢዎች ተፈናቅለው የነበሩ እና በዘንደሮ ዓመት ወደ ቀአቸው የተመለሱ ናቸው፡፡ የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ተሲሳ ለ «DW»  እንደተናገሩት  በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅሉ የነበሩ እና በጽ/በታቸው መዝገብ የሚታወቁ   ዜጎች ሙሉ በሙሉ ወደ ቀድሞ ቀአቸው ተመልሰው ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚገንኝ ሲሆን በርካቶችም መደበኛ የእርሻ ስራቸውን ማከናወን ጀምሯል፡፡  ከሳምንት በፊት በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ተፈጥሮ በነበሩበት አለመግባባቶችም አንድ ሺ የሚደርሱ ዜጎች ተፈናቅለው በተለያዩ ስፋራዎች ተጠልሎ እንሚገኙና በተቋማቸው በኩል ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ 
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ተፈናቅለው ከነበሩት እና በግንቦት ወር ወደ ቀአቸው ከተመለሱት መካከል አቶ መሰረት አንዱ ሲሆኑ በወረዳው አንድ አንድ የገጠር መንደሮች ለተመለሱ ተፈናቃዩች ድጋፍ መደረጉን  ተናግረዋል፡፡ በማንዱራ ከተማ ለሚገኙ ተመላሾች ደግሞ  ምንም ዓይነት ድጋፍ አልተሰጠም ብለዋል፡፡ በገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ የወደመባቸው ሰዎች መኖራቸውንም እና ወደ ከተማ የተመለሱ እንዳሉም አክለዋል፡፡ ሌላው የማንዱራ ተመላሽም በሰጡን አስተያየት ያለምንም ስጋት መንቀሳቀስ እንዲንችል የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታን በመጠበቅ ነዋሪው የግብርና ስራውን በወቅቱ እንዲያከናውን  ኮማድ ፖስቱ እገዛ ሊደርግልን ይገባል ብለዋል፡፡
የክልሉ የአደጋ ስጋት  አመራር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታቀኝ ተሲሳ  ቤት የተቃጠለባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች በተገኘው ድጋፍ በመተከል ዞን እና ካማሺ ዞን  9ሺ የሚደርሱ  የመኖሪያ ቤቶችም መገንባታቸውን    አመልክቷል፡፡   በዘላቂነት ከተቋሙ በኃላም ለአንድ ዓመት እና ከዛ በላይ ለሚሆን ጊዜያት ድጋፍ ሲያኙ የነበሩ ተመላሾች ራሳቸውን  እንዲችሉ የሚሰጡ እርዳታዎች  ይቋረጣሉ ብለዋል፡፡

Äthiopien Ato Tarekegen Tesisa | Leiter  Katastrophen- und Risikomanagement Region Benishangul gumuz
ምስል DW/Negassa Dessalegn

 

ነጋሳ ደሳለኝ 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ