1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባልደራስ አመራሮች የክስ ሂደት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 4 2014

የባልደራስ የክስ ሂደትን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ለነገ ተአጠረ። ችሎቱ ዐቃቤ ሕግ ነገ ምስክሮችን ይዞ እንዲቀርብ አዟል። ዐቃቤ ሕግ በዛሬው ችሎቱ ሁለት ምስክሮች ቃላቸውን እንደሚሰጡ ለፍርድ ቤቱ ተናግሮ ነበር።

https://p.dw.com/p/41gFa
Der Parteiführer von Balderas traf sich mit Bewohnern von Bahrdar
ምስል DW/A. Mekonnen

ችሎቱ ዐቃቤ ሕግ ነገ ምስክሮችን ይዞ እንዲቀርብ አዟል

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አመራሮችን የክስ ሂደት የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ለዛሬ ይዞት የነበረውን ምስክሮችን የማድመጥ ሂደት ለነገ በማድረግ ተጠናቋል።  ችሎቱ ዐቃቤ ሕግ ነገ ምስክሮችን ይዞ እንዲቀርብ አዟል። ዐቃቤ ሕግ በዛሬው ችሎቱ ሁለት ምስክሮች ቃላቸውን እንደሚሰጡ ለፍርድ ቤቱ ተናግሮ ነበር።

ሆኖም የተከሳሽ ጠበቆች በዛሬው ችሎት አራት ምስክሮች መቅረብ እንደነበረባቸው እና የምስክሮች ስም ዝርዝር ለተከሳሾች እና ጠበቆች መድረስ ሲገባው እንዳልደረሳቸው በመግለፅ ተከራክረዋል።

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የምስክሮች ዝርዝር ለተከሳሾች እና ጠበቆች እንዲደርስ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመስጠቱን በመጥቀስ ተከራክሯል። ግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ችሎቱ ዐቃቤ ሕግ ነገ ምስክሮቹንና የምስክሮቹን ዝርዝር ይዞ እንዲቀርብ አዟል። በአዲስ የተሰየሙት ዳኞች የጉዳዩን ዝርዝር ዶሴ ገና አለማንበባቸውን ጠቅሰው ከተከሳሾች ሁለት የመብት ጥያቄዎችን አድምጠው ችሎቱ ነገ ረፋድ እንዲቀጥል ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ