1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባልደራስ በርካታ አባላቱና የሰልፉ አስተባባሪዎች ታሰሩ

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 1 2012

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነገው ዕለት በከተማይቱ በሚገኘው የመስቀል አደባባይ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ እንደሌለ አስታወቀ። ለነገ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ የነበረው የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) በበኩሉ በርካታ አባላቱ እና የሰልፉ አስተባባሪዎች ዛሬ መታሰራቸውን ገልጿል።

https://p.dw.com/p/3RBiU
Äthiopien Addis Abeba | Journalist Eskindir Nega bei Presskonferenz
ምስል DW/S. Muchie

ለነገ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ የነበረው የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) በርካታ አባላቱ እና የሰልፉ አስተባባሪዎች ዛሬ መታሰራቸውን ገለፀ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ደግሞ በነገው ዕለት በከተማይቱ በሚገኘው የመስቀል አደባባይ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ የለም ብሏል።  
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጹ ዛሬ ይፋ እንዳደረገው በነገው ዕለት በሚኖረው ሰልፍ ምክንያት የሚዘጉ መንገዶች እንደሚኖሩ ፖሊስ ኮሚሽኑ እንደገለጸ ተደርጎ የተላለፈው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል። የከተማይቱ ነዋሪ በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ የሌለ እና ምንም የሚዘጋ መንገድ አለመኖሩን ተገንዝቦ መደበኛ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚችል ፖሊስ ኮሚሽኑ አሳስቧል። 
የነገውን ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው በጋዜጠኛ እና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) በዛሬው ዕለት በበርካታ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ ላይ የእስር ዘመቻ መደረጉን አስታውቋል። እስካሁን ምን ያህል ሰዎች በትክክል እንደታሰሩ እንደማይታወቅም አቶ እስክንድር ለ DW ተናግረዋል።   

ሰለሞን ሙጬ /ተስፋለም ወልደየስ

ልደት አበበ