1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባልደራስ ሰላማዊ ሰልፍ መከልከል የአምባገነንነት ጅማሬ ማሳያ ተባለ

ሰኞ፣ ጥቅምት 3 2012

የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት «ባልደራስ » እያለ የሚጠራዉ ስብስብ ትናንት እሁድ መዲና አዲስ አበባ ላይ የጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ መከልከሉ በሀገሪቱ የታየዉን የዴሞክራሲ ጭላንጭል የሚያዳፍን ነዉ ሲሉ በከተማዋ የሚገኙ ነዋሪዎች ገለፁ።

https://p.dw.com/p/3RGVG
Flash-Galerie Der Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል S. Mengist

በሕጉ መሰረት ፖሊስ መከልከል አይችልም

የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት «ባልደራስ » እያለ የሚጠራዉ ስብስብ ትናንት እሁድ መዲና አዲስ አበባ ላይ የጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ መከልከሉ በሀገሪቱ የታየዉን የዴሞክራሲ ጭላንጭል የሚያዳፍን ነዉ ሲሉ በከተማዋ የሚገኙ ነዋሪዎች ገለፁ። ዶይቼ ቬለ «DW » ያነጋገራቸዉ አንድ የሕግ ባለሞያ እና አንድ ታዋቂ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ የከተማ አስተዳደሩ የፈቀደዉን ሰላማዊ ሰልፍ ፖሊስ መከልከሉን በማዉገዝ ድርጊቱን የአምባገንንነት ጅማሬ  ማሳያ ሲሉ ገልፀዉታል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዝርዝሩን ይዞአል።  


ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ