1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሌ ክልል ባለሥልጣናት ሽኩቻ

ዓርብ፣ መጋቢት 25 2012

በሶማሌ ክልል ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች መካከል ልዩነት መኖሩን አንድ የክልሉ ቀድሞ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ገለፁ፡፡ የርዕሰ መስተዳድሩ ፕሮቶኮል እና የፀጥታ አማካሪ መታሰራቸውን እንደሚያውቁ ተናግረዋል ፡፡

https://p.dw.com/p/3aPnB
Äthiopien Stadt Jijiga
ምስል DW/T. Waldyes

በክልሉ ፀጥታ ኃላፊ ላይ ርምጃ ተወስዶአል

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ላይ የተደረገ የመንፈቅለ መንግስት ሙከራ ከሸፈ በሚል ትናንት በተለያዩ መረጃዎች የተፈጠረውን ሁኔታ አስመልክቶ ለ«DW» በስልክ መረጃ የሰጡት የክልሉ ቀድሞ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አህመድ ጌዲ በፖለቲካ አመራሩ ልዩነት መኖሩንና ይኸው ጫፍ ደርሶ በክልሉ ፀጥታ ኃላፊ ላይ ርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል። አቶ አህመድ በክልሉ አሁን ላይ ተንሰራፍቶ የሚታየው አስተዳደራዊ እና የሙስና ችግር እና የሚተገበሩ ስራዎች የልዩነት መነሻ መሆኑን ገልፀው ርዕሰ መስተዳድሩ ተገቢውን አመራር እየሰጡ እና እርምጃም እየወሰዱ አይደለም ብለዋል። በሶማሌ ክልል አለ ከተባለው የፖለቲካ አመራሩ እሰጥ አገባ ጋር እና ወቅታዊ ችግር ጋር በተያያዘ የርዕሰ መስተዳድሩ ፕሮቶኮል ኃላፊ እና የፀጥታ አማካሪ መታሰራቸውን ተናግረዋል፡፡ የፀጥታ ኃላፊው ከኃላፊነት መነሳታቸውን ጠቁመዋል። በተመሳሳይ መልኩ በክልሉ ስራ አስፈፃሚ መካከል አለ ከተባለው ልዩነት ጋር በተያያዘ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አደም ፋራህ ከክልሉ ወተዋል በሚል የሚናፈሰው ወሬም ትክክል አይደለም ሲሉ ገልፀዋል። በክልሉ አሉ በተባሉት ጉዳዮች ዙርያ የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ እና ሌሎች ባለስልጣናትን ለማነጋገር እና አስተያየት እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ብንሞክረም አልተሳካም ፡፡

መሳይ ተክሉ 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ