1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡድን 20 ጉባዔና ፍትኃዊ የኮሮና ክትባት ተጠቃሚነት

ሰኞ፣ ኅዳር 14 2013

ቡድን 20 በመባል የሚታወቁት በኤኮኖሚ የበለፀጉት ሃገራት ጉባዔ የኮሮና ተኅዋሲን ለመከላከል በቀረበዉ ክትባት ፍትኃዊነት እንዲረጋገጥ ተጠየቀ። በኢንተርኔት አማካኝነት በተካሄደዉ እና ሳዉዲ አረብያ በመራችዉ የሁለት ቀናት ጉባዔ ክትባቱ ለድሆች ሃገራት በፍትኃዊነት ማዳረሱ ኮሮና ተኅዋሲን ከዓለም ለማጥፍት አንዱ መፍትሄ ነዉ ተብሎአል።

https://p.dw.com/p/3lioG
Virtueller G20-Gipfel | Russland
ምስል Alexei Nikolsky/dpa/picture alliance

ክትባትን በፍትኃዊነት ለማዳረስ ድጋፍ ተጠይቆአል

ቡድን 20 በመባል የሚታወቁት በኤኮኖሚ የበለፀጉት ሃገራት ጉባዔ የኮሮና ተኅዋሲን ለመከላከል በቀረበዉ ክትባት ፍትኃዊነት እንዲረጋገጥ ተጠየቀ። በኢንተርኔት አማካኝነት በተካሄደዉ እና ሳዉዲ አረብያ በመራችዉ የሁለት ቀናት ጉባዔ ክትባቱ ለድሆች ሃገራት በፍትኃዊነት ማዳረሱ ኮሮና ተኅዋሲን ከዓለም ለማጥፍት አንዱ መፍትሄ ነዉ ተብሎአል። የኮሮና ተኅዋሲ ክትባትን በፍትኃዊነት ለማዳረስ እንዲያስችል የአዉሮጳ ኅብረት እና ሌሎች መሪዎች የገንዘብ ልገሳ እንዲያደረግ ጠይቀዋል። የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ድሆች ሃገራት የኮሮና ክትባት ፍትኃዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲወተዉቱ መቆየታቸዉ ይታወቃል። የጉባዔዉ ዋንኛ መነጋገርያ በአብዛኛዉ የኮሮና ተኅዋሲና መከላከያዉ ላይ ይሁን እንጂ፤ የበለፀጉት ሃገራት መሪዎች የዓለም አየር ንብረት ለዉጥን መከላከል ፤ የዓለም የንግድ ልዉዉጥ እና የቀረጥ ጉዳይ የጉባዔዉ ሌላ የመነጋገርያ አጀንዳ ነበር።   
 

ይልማ ኃይለሚካኤል  

አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ