የቡሽ ስንብት
ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2011ማስታወቂያ
የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆርጅ ሐርበርት ዎከር ቡሽ (ትላቁ) ዛሬ ባገሬዉ አቆጣጠር ቀትር ላይ (ከአንድ ሰዓት በኋላ ማለት ነዉ) ሁስተን ቴክሳስ ዉስጥ ይቀበራሉ።አርባ አንደኛዉ የዩናትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ያረፉት ባለፈዉ አርብ ነበር።አስከሬናቸዉ ባለፈዉ ሰኞ ወደ ዋሽግተን ተጉዞ እስከ ትናንት ድረስ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ተሰናብቶታል።ትናንት በነበረዉ የስንብት ሥነ-ሥርዓት ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ያሁኑ ፕሬዝደንት፣ በሕይወት ያሉ የቀድሞ ፕሬዝደንቶች፤ የዉጪ ሐገራት መሪዎች እና ተጠሪዎች ሟቹን ተሰናብተዋል።ቡሽ 94 ዓመታቸዉ ነበር።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ