1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበኒ ሻንጉል ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ዉዝግብ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 15 2011

የበኒ ሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ለሠላምና ለዴሞክራሲ (በሕነንሠዴ) የተሰኘዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የክልሉ መስተዳድር የፓርቲዉን መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች ያስራል፣ፓርቲዉ እንዳይንቀሳቀስ ያዉካል በማለት ወቀሰ

https://p.dw.com/p/3HISa
Asosa, West-Äthiopien und Hauptstadt der Region Benishangul-Gumuz
ምስል privat

የበኒ ሻንጉል የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉዝግብ

ምዕራብ ኢትዮጵያ በኒ ሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር የሚንቀሳቀሰዉ የበኒ ሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ለሠላምና ለዴሞክራሲ (በሕነንሠዴ) የተሰኘዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የክልሉ መስተዳድር የፓርቲዉን መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች ያስራል፣ፓርቲዉ እንዳይንቀሳቀስ ያዉካል በማለት ወቀሰ።የፓርቲዉ መሪዎች እንደሚሉት በቅርቡ ብቻ 6 የፓርቲዉ ባለስልጣናት ታስረዋል።የበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ገዢ ፓርቲ ግን የተቃዋሚዉ ፓርቲን ወቀሳ አልተቀበለዉም።የገዢዉ ፓርቲ መሪዎች እንደሚሉት ሰዎቹ የታሰሩት ግለሰብ ስለከሰሳቸዉ ነዉ።

ነጋሳ ደሳለኝ 

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋለም ወልደየስ