የበረሐ አንበጣ ጉዳት በኢትዮጵያ
ዓርብ፣ መስከረም 22 2013ማስታወቂያ
የአፋር፣ የአማራና የትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎችን የወረረዉ የበረሃ አንበጣ መንጋ አሁንም በሰብልና ደን ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገበሬዎችና የግብርና ባለሥልጣናት አስታወቁ። በቀይ ባሕር ዳርቻዎች እንደተፈለፈለ የሚገመተዉ የአንበጣ መንጋ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የግብርና ምርት 3.5 ሚልዮን ኩንታል የሚሆነውን ማውደሙን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡ መንጋዉን በፍጠነት መከላከል ካልተቻለ በዘንድሮዉ የምርት ዘመንም ከፍተኛ ሰብልና ደን ያጠፋል የሚል ሥጋት አሳድሯል። የግብርና ሚኒስቴር ባለሥልጣናት እንደሚሉት ግን መሥሪያ ቤታቸዉ የአንበጣዉን ሥርጭትና የሚያደርሰዉን ጉዳት ለመከላከል እየጣረ ነዉ። ግብርና ሚንስቴር ለሚያደርገዉ ጥረት የዓለም የእርሻና ምግብ ድርጅት (FAO) ድጋፍ እንዳልተለየዉም ባለሥልጣናቱ አስታዉቀዋል።
ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ
ነጋሽ መሐመድ