1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ኮሮና ያሳደረዉ ተጽእኖ

ዓርብ፣ መጋቢት 25 2012

የኮሮና ተህዋሲ ሥርጭትን ለመከላከል የተጣሉ የአውሮፕላን በረራ እገዳዎች ከምሥራቅ አፍሪቃ የበረሃ አንበጣ ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን የዓለም የምግብና እርሻ  ድርጅት (FAO) አሳሰበ።

https://p.dw.com/p/3aQNd
Pakistan Kinder versuchen Heuschrecken zu verjagen
ምስል picture-alliance/AP/S. Baluch

የኮሮና ተህዋሲ ሥርጭትን ለመከላከል የተጣሉ የአውሮፕላን በረራ እገዳዎች ከምሥራቅ አፍሪቃ የበረሃ አንበጣ ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን የዓለም የምግብና እርሻ  ድርጅት (FAO) አሳሰበ። ድርጅቱ እንዳለው በበረራ እገዳ እና ክልከላዎች ምክንያት የሚረጩ መድኃኒቶች አቅርቦት ዘግይቷል። በአሁኑ ጊዜ የበረሃ አንበጣን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት በመድሐኒት እጥረት ምክንያት ከተደናቀፈ፣ ከ4 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ቤተሰቡን መመገብ አይችልም። ኬንያ መጋዘን ዉስጥ የተቀመጠው መድኃኒት ከቀናት በኋላ ያልቃል። አንበጣ በዚህ ዓመት የመን፣ ኬንያ፣ ሶማሊያና ኢትዮጵያን ክፉኛ ጎድቷል። በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት መንግሥታት ድንበሮቻቸውን ከመዝጋታቸውም በላይ የእቃ ጫኝ አውሮፕላኖች በረራዎችንም ቀንሰዋል። ይህም የበረሃ አንበጣን ለማጥፋት የሚረጨውን መድኃኒት ዓለም አቀፍ አቅርቦት ያናጋ ሲሆን በአውሮጳ እና በእስያም የመድኃኒቱ ምርት እንዲቀንስ አድርጓል። 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ