1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 22 2011

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የጥቅምት ጉባኤውን መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ። ለአስር ቀናት በዝግ የተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ በሁለት ዓበትይ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

https://p.dw.com/p/37WyV
Äthiopien Synode | Patriarch Matias
ምስል DW/Getachew Tedla

የቅዱስ ሲኖዶስ የጥቅምት ጉባኤ ተጠናቀቀ

ቅዱስ ሲኖዶሱ በመግለፃው በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም የዜጎች መፈናቀል እና መሰል ችግሮች መኖራቸው እንደሚሰማ እና ለዚህም አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግ መንግሥት ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቋል። ከዚህም ሌላ በኢየሩሳሌም ከሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማት በአንደኛው ማለትም በዴር ሡልጣን የሚገኘውን ገዳም ለማደስ የተጀመረው እንቅስቃሴ እና  ከግብፅ ቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ጋር የተገባውን ውዝግብም አንስቷል።  ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ