1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞ የሰገን ዞን የመንግሥት ሠራተኞች አቤቱታ

ረቡዕ፣ መስከረም 14 2012

ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አቤቱታቸውን ለማቅረብ ወደ ሀዋሳ የመጡት ሠራተኞች ለዶቼ ቨለ እንዳሉት ዞኑ በፈረሰበት ወቅት ከክልል ጀምሮ በመረጡባቸው ዞኖችና ወረዳዎች እንደሚመደቡ በክልሉ ባለስልጣናት ተገልጾላቸው ነበር። ይሁንእንጂ እስከአሁን የስራ ምደባው አልተሰጣቸውም ፣ ወርሃዊ ደሞዛቸውም ከባለፈው ሐምሌ ጀምሮ ተቋርጦባቸዋል።

https://p.dw.com/p/3QEqy
Äthiopien | Ato Dawit Hailu stellvertretender Leiter des öffentlichen Dienstes der SNNP
ምስል DW/S. Wegayehu

የቀድሞ የሰገን ዞን የመንግሥት ሠራተኞች አቤቱታ

በደቡብ ክልል ከወራት በፊት በፈረሰው የሰገን ህዝቦች ዞን ሲያገልግሉ የነበሩ ከአምስት መቶ በላይ ቋሚ የመንግስት ሰራተኞች የክልሉ መንግስት ቃል የገባልንን የስራ ምደባ ገቢራዊ ባለማድረጉ ከነቤተሰቦቻችን ችግር ላይ ወድቀናል አሉ። ለክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አቤቱታቸውን ለማቅረብ ወደ ሀዋሳ የመጡት እነኝሁ ሰራተኞች ለዶቼ ቨለ ( DW ) እንዳሉት ዞኑ በፈረሰበት ወቅት ከክልል ጀምሮ በመረጡባቸው ዞኖችና ወረዳዎች እንደሚመደቡ በክልሉ ባለስልጣናት ተገልጾላቸው ነበር። ይሁን እንጂ እስከአሁን የስራ ምደባው አልተሰጣቸውም ፣ ወርሃዊ ደሞዛቸውም ከባለፈው ሐምሌ ጀምሮ ተቋርጦባቸዋል። እንኳን ያለደሞዝ ደሞዝ ተከፍሎም ቢሆን የኑሮን አስቸጋሪነት እንረዳለን ያሉት የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው የሰራተኞቹ የስራ ድልድልና የደሞዝ በጀትን ቢያንስ በአጭር ቀናት ውስጥ በማጠናቀቅ ምላሽ ለመስጠት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። ዝርዝሩን የሀዋሳው ወኪላቸን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ልኮልናል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

Äthiopien | Beamter: Demese Dejene
ምስል DW/S. Wegayehu