1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀረጥ ቅናሽ ለኤሌክትሪክ መኪኖች

ማክሰኞ፣ መስከረም 17 2015

እነኝህ ዘመናዊ እና የኤሊክትሪክ መኪኖች በአዲስ አበበ መንገዶች መታየታቸው ከግዜ ወደግዜ እየጨመረ መጥቶዋል። እንዳነጋገርኩዋቸው ሰዎች ሀሳብ ከሆነ ግን ጥቂት የከተማዋ ተረኛ ሀብታሞች የሚጠቀሙበት ከምሆን ባሻገር አሁን ባለው የሀገራችን መንገድ እና የመብራት ሀይል አቅም እንደታሰበው ለውጥ የሚመጣ የሚሆን አይመስልም።

https://p.dw.com/p/4HPxb
Berlin Gipfel Elektromobilität
ምስል AP

ለመብራት የሚጠፋዉ ኤሌክትሪክ ለመኪና ይገኝ ይሆን?

                         
ኢትዮጵያ መንግስት በኤሌክትሪክ ኃይል በሚሽከረከሩ መኪኖች ላይ የቀረጥ ቅናሽ ማድረጉን ሰሞኑን አስታዉቋል።የገንዘብ ሚንስቴር እንዳስታወቀዉ ሐገር ዉስጥ በሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የ15 በመቶ፣ ከዉጪ በሚገቡት ላይ ደግሞ የ5 ከመቶ የቀረጥ ቅናሽ አድርጓል።መንግስት ቅናሹን ያደረገዉ የንዳጅ ዋጋ ንረት እና የዓየር ንብረት ብክለትን ለመቀነስ ነዉ።ለመብራት የሚጠፋዉ ኤሌክትሪክ ለመኪና ይገኝ ይሆን?

በአለም ላይ እየታየ ያለውን የአየር ንብረት ብክለት ለመቀነስ በሚል በቅርቡ  መንግስት በተወሰኑ መኪኖች ላይ የቀረጥ ቅናሽ አድርጎዋል ።  
የገንዘብ ሚንስትር ያስታወቀው የቀረጥ ቅነሳ የተደረገባቸው መኪኖች የኤሊክትሪክ መኪኖች ናቸው እነኝህ የኤሊክትሪክ መኪኖች ከውጭ የሚገቡትም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙት ሁሉ የቀረጥ ቅነሳው ይመለከታቸዋል ስራቸው ባብዛኛው አልቆ   በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ የኤሊክትሪክ መኪኖች ላይ 15 % ከውጭ በሚገቡት የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ደግሞ የ5% የታክስ ቅናሽ ተደርጎዋል ።
በኢትዮጵያ በአጭር ግዜ ውስጥ የቀን ተቀን ኑሮ ላይ የሚያስፈልጉ  ቁሳቁስ  እና መገልገያዎች ዋጋ ከ 100% በላይ ጨምሮዋል። ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ዋጋ ንረት  የተለመደው የመቶኛ ጭማሪ ብቻውን አይገልፅውም። 
መንግስት የነዳጅ ዋጋ ድጎማውን እንደሚያነሳ ካሳወቀበት እና ተግባራዊ ካደረገበት ግዜ ጀምሮ የትራንስፖርት ዘርፉ በዋጋ ንረት ሲናውጥ ቆይትዋል ይህንን ለማርገብ የተወሰደው የቀረጥ ቅነሳ በጎ ቢሆንም ለችግሩ አፋጣኝ  መላ የሚሆን አይመስልም ።እነኝህ ቅናሽ ተደርጎባቸዋል የተባሉት የኤሊክትሪክ መኪኖች  በተማው  አለፍ ብሎም በሀገሪቱ ያለውን የትራንስፖርት ችግር እና የመኪና ዋጋን ይቀንስ እንደሆን ወደፊት የሚታይ ቢሆንም ፣DW ያነጋገራቸው ሰዎች ግን ‘ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ነው  መብራቱን በቅጡ ሁሉም ቦታ ባገኘነው ‘መንግስት  ቅናሽ ሊያደርግባቸው የሚገባ  ኑሮዋችንን የበለጠ የሚያቀሉ ብዙ  ነገሮች አሉ ይላሉ ።

እነኝህ ዘመናዊ እና የኤሊክትሪክ መኪኖች በአዲስ አበበ መንገዶች መታየታቸው ከግዜ ወደግዜ  እየጨመረ መጥቶዋል። እንዳነጋገርኩዋቸው ሰዎች ሀሳብ ከሆነ ግን ጥቂት የከተማዋ ተረኛ ሀብታሞች የሚጠቀሙበት ከምሆን ባሻገር አሁን ባለው የሀገራችን መንገድ እና የመብራት ሀይል አቅም እንደታሰበው ለውጥ የሚመጣ የሚሆን አይመስልም።

ሐና ደምሴ 

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ