1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶስቱ የትግራይ ቴሌቪዥኖች ስርጭት መቋረጥ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 30 2012

የስርጭት ማዕከላቸውን በመቀሌ ከተማ አድርገው ያስተላልፉ የነበረ መንግስታዊውን የትግራይ ቴሌቪዥንን ጨምሮ ሶስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከትናንት ጀምሮ ስርጭታቸው ቢቋረጥም ድምጸ ወያኔ ቴሌቪዥን በሌላ ሳተላይት በከፊል መመለሱ እየተነገረ ነው።

https://p.dw.com/p/3euoM
Thema Digitalisierung des bulgarischen Fernsehens
ምስል BGNES

የትግራይ ቴሌቪዥን እና ድምጸ ወያኔ ስርጭታቸው ተቋረጠ

የስርጭት ማዕከላቸውን በመቀሌ ከተማ አድርገው ያስተላልፉ የነበረ መንግስታዊውን የትግራይ ቴሌቪዥንን ጨምሮ ሶስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከትናንት ጀምሮ ስርጭታቸው ቢቋረጥም ድምጸ ወያኔ ቴሌቪዥን በሌላ ሳተላይት በከፊል መመለሱ እየተነገረ ነው። የትግራይ ቴሌቪዥን እና የድምጸ ወያኔ የስራ ሃላፊዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከፈረንሳይ መንግስት ጋር ባደረጓቸው ስምምነቶች ስርጭቱ እንዲቋረጥ መደረጉን ገልጸዋል። የቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ስርጭት መቋረጥ እና የመንግስትን ምላሽ የጠየቀውን የመቀሌው ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለስላሴን አነጋግሬዋለሁ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ