1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሌ ክልል መንግስት አዲስ ተመሰረተ

ሰኞ፣ ጥቅምት 8 2014

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መስራች ጉባዔው ላለፉት ሶስት ዓመታት ክልሉን በምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት ሲመሩ የቆዩትን አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ዑመርን ርዕሰ መስተዳድር ፤ አቶ ኢብራሂም ዑስማን ፋራህን ምክትል ርዕሰ ስተዳድር አድርጎ ሾሟል፡፡

https://p.dw.com/p/41pDz
Äthiopien Somale Regional Council
ምስል Messay Teklu/DW

የሶማሌ ክልል መንግስት አዲስ መመስረቱ

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መስራች ጉባዔው ላለፉት ሶስት ዓመታት ክልሉን በምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት ሲመሩ የቆዩትን አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ዑመርን ርዕሰ መስተዳድር ፤ አቶ ኢብራሂም ዑስማን ፋራህን ምክትል ርዕሰ ስተዳድር አድርጎ ሾሟል፡፡ በተጫማሪም ጉባዔው ወ/ሮ አያን አብዲን የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ እንዲሁም አቶ ኢብራሂም ሀሰን አሊን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ ሾሟል፡፡ ላለፉት ሶስት ዓመታት በለውጥ ሂደት አልፎ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ኃላፊነት የተረከበው የክልሉ መንግስት በተለያዩ መስኮች ለውጥ ያመጣል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ለዶይቼ ቬሌ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ 

መሳይ ተክሉ
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ