1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስፖርት ጥንቅር፤ ሰኞ ሐምሌ 6፣ 2012 ዓ.ም

ሰኞ፣ ሐምሌ 6 2012

ከ 30 ዓመት በኋላ የእንጊሊዝ ፕሬሜር ሊግ ሻፕዮን መሆኑን አስቀድሞ ያረጋገጠዉ ሊቨርፑል በሜዳዉ ያለመሸነፍ ክብረ-ወሰን ለመስበር የነበረዉ ምኞት ሳይሳካ ቀርቶአል። የእንጊሊዝ ፖሊስ ለአንድ የፕሬሜር ሊግ ተጫዋች ዘረኝነት የተላበሰ አሳፋሪ መልክት በማኅበራዊ መገናኛ ዘደዎች አስተላልፎአል ያለዉን አንድ ታዳጊ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታዉል።

https://p.dw.com/p/3fGYu
Premier League - Norwich City v Brighton & Hove Albion
ምስል Reuters/R. Heathcote

የስፖርት ጥንቅር፤ ሰኞ ሐምሌ 6፣ 2012 ዓ.ም


ከ 30 ዓመት በኋላ የእንጊሊዝ ፕሬሜር ሊግ ሻፕዮን መሆኑን አስቀድሞ ያረጋገጠዉ ሊቨርፑል በሜዳዉ ያለመሸነፍ ክብረ-ወሰን ለመስበር የነበረዉ ምኞት ሳይሳካ ቀርቶአል። ቼልሲ አሳዛኝ ሽንፈት ያስተናገደበት 35 ኛዉ ሳምንት የፕሬሜር ሊጉ የጨዋታ መረሃ -ግብር ማንችስተር ሲቲ በራሂም ስተርሊን ሃትሪክ የተስተናገደበት እና በግብ ተንበሽብሾ የወጣበት ሳምንት ሆኖም አልፎአል። የእንጊሊዝ ፖሊስ ደግሞ ለአንድ የፕሬሜር ሊግ ተጫዋች ዘረኝነት የተላበሰ አሳፋሪ መልክት በማኅበራዊ መገናኛ ዘደዎች አስተላልፎአል ያለዉን አንድ ታዳጊ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታዉል።  በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ተወዳዳሪ የሆነዉ ፤ ዩኒየን በርሊን ደግሞ በቀጣዩ የዉድድር ዘመን ያለተመልካች በባዶ ስታድየም ዉድድር ከማድረግ የኮሮና ተኅዋሲ ምርመራ አድርገዉ ፤ ከቫይረሱ ነፃ ሆኑ ደጋፊዎቹን ቡድናቸዉን ለመደገፍ ስታድየም እንዲታደሙ ለማድረግ መዘጋጀቱን ይፋ አድርጎአል። በዚህ የእስፖርት ቅንብራችን ይህንን እና የተለያዩ አጫጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች የተካተቱበት ነዉ። 


ሃይማኖት ጥሩነህ     
አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ