በካሌ አስከፊዉ የስደተኞች ሕይወት፤
ዓርብ፣ ሐምሌ 22 2008ማስታወቂያ
ከካሌ ከተማ የተወሰኑ ኪሌ ሜትሮች ወጣ ብሎ የሚገኘዉ የስደተኞቹ ጊዜያዊ መጠለያ ጫካ በአሁኑ ሰዓት ከ7 እስከ 8 ሺህ የሚገመቱትን ያስተናግዳል። ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት እንዲፈርስ የተደረገ ሲሆን በቅርቡም የከተማዉ አስተዳደር እንደሚያፈርሰዉ እየተነገረ ነዉ። ከዚህም ሌላ በስደተኞቹ መጠለያ ዙሪያ 4 ሜትር ርዝመት ያለዉ ግምብ ለማስገምባትም ዕቅድ መንደፉም ተሰምቷል። በፕላስቲክ ድንኳኖች እና በተለያዩ ቁሳቁሶች የተገነባዉ የስደተኞቹ መጠለያ መሠረታዊ ነገሮች ባይሟሉለትም የንግድ የእምነት ተቋማት እና ቤተ መጻሕፍትም ታክለዉበታል። ሰሞኑን ወደስፍራዉ ተጉዛ የነበረችዉ የፓሪሷ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች። ከዚህ ስፍራ በሌሊት ተነስተዉም በከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ በድብቅ በመጫን ወደሚመኟት እንግሊዝ ለመግባት ሲሞክሩም በርካቶቹ ሕይወታቸዉን በአሳዛኝ ሁኔታ አጥተዋል። በቅርቡ በዚህ ሁኔታ ያለፈችዉን ጨምሮ ካለፈዉ ጥር ወር አንስቶ በተመሳሳይ መንገድ ሕይወታቸዉ ያለፈ ስደተኞች ቁጥር ከስምንት እንደሚበልጥ ተሰምቷል። በሌላ በኩልም በስደተኞች መካከል በሚፈጠረዉ የእርስ በርስ ግጭት ሳቢያም ሕይወት እየጠፋ ይገኛል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ