የስቅለት አከባበር በኢትዮጵያ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 22 2013ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን እና ምዕመናን ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን እለት በስግደት እና በፆም በፀሎት አክብረዉት ዉለዋል። ቤተክርስቲያኒቱ ርእሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እና ምዕመናን በታደሙበት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ የምህላና የፀሎት ሥነ-ስርዓት ተከናውኗል። ርእሰ-ሊቃነጳጳሳቱ በዚሁ ወቅት ሃይማኖታዊ ትምህርት እና ቡራኬንም ሰጥተዋል። በሃማኖታዊ ስርዓቱ የታደሙ ምዕመናንም ለወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ በአንድነት መቆምና አብዝቶ መፀለይ ይገባልም ብለዋል፡፡
ሥዩም ጌቱ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ