1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሴቶች የፖለቲካ አመራር የጋራ ምክር ቤት ተቋቋመ

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 29 2013

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስተባባሪነት የተቋቋመው ይኽ ምክር ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎች የሴቶችን ተሳትፎ እና የመሪነት ሚና አጉልቶ ለማሳየት ፣ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በሁሉም መስክ ለማረጋገጥ ይሠራል ተብሏል።

https://p.dw.com/p/3zsjR
Äthiopien Wahl 2021 | Wahllokal Addis Abeba
ምስል Ben Curtis/AP Photo/picture alliance

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስተባባሪነት ነው የተቋቋመው

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሴት አመራር አባላት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስተባባሪነት የጋራ ምክር ቤት አቋቋሙ። ምክር ቤቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሴቶችን ተሳትፎ እና የመሪነት ሚና አጉልቶ ለማሳየት ፣ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በሁሉም መስክ ለማረጋገጥ ይሠራል ተብሏል ።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሥራ ላይ እያለ ሌላ የሴት የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የጋራ ምክር ቤት ማቋቋሙ ተገቢነት ላይ ጥያቄ ተነስቶበት ነበር። ሆኖም የሴቶችን ተሳትፎ የላቀ ለማድረግ አስፈላጊ ነው በሚል ምክር ቤቱ ተመስርቷል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የቢሮ እና ሌሎች ድጋፎችን ያደርግለታል ተብሏል።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ