የዓለም የሴቶች ቀን
ሰኞ፣ የካቲት 29 2013ማስታወቂያ
የሴቶች የኑሮ ትግልና ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን
የሴቶች መብትና እኩልነት የሚዘክረው የዓለም የሴቶች ቀን ዛሬ ማለትም በጎርጎሮሲያኑ መጋቢት 8 በተለያዩ የዓለም ሃገራት ታስቦ ዉሏል። እንደ ፓኪስታን፣ አውስትራሊያ እና ቱርክ ባሉ ሀገራት ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች አደባባይ በመውጣት በሴቶች ላይ የሚደርስን ጥቃት አውግዘዋል ፣ ፆታዊ እኩልነታቸው እንዲከበርም ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ ውስጥም ይህንን ቀን አስመልክቶ ትናንት እሁድ የመንግስት አመራሮች፣ ታዋቂ አትሎቶች እና አርቲስቶች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የተካፈሉበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል። እንደዛም ሆኖ ይህ ቀን ለምን ታስቦ እንደሚውል የማያውቁ ሴቶች አሉ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰለሞን ሙጬ ዝቅተኛ ገቢ በሚያስገኝ ሥራ ላይ ተሰማርተው ሕይወትን የሚመሩ ሦስት ሴቶችን ሥለ ሥራና አኗኗራቸው ጠይቆ ተከታዮን ዘገባ ልኮልናል።
ሰለሞን ሙጬ
ልደት አበበ
አዜብ ታደሰ