የሳዑዲ አረብያ እና የኢትዮጵያ የሠራተኞች አላክና አቀባበል ስምምነት
ማክሰኞ፣ ግንቦት 20 2011ማስታወቂያ
ሳዑዲ አረብያ ከኢትዮጵያ የሚመጡ የቤት ሠራተኞችን መቀበል አቆመች። ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ የቤት ሠራተኞች ለመላክ ሳዑዲ አረብያ ለመቀበል ተስማምተው ነበር። ሳዑዲ ጋዜት እንደዘገበው ግን አሁን ከተያዘው የረመዳን ወር በፊት ኢትዮጵያ ሠራተኞችን ባለመላኳ ውሉ እንዲቋረጥ ተደርጓል። ዶይቼቬለ DW ስለ ጉዳዩ የጠየቀው በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሥልጣናት ግን የሥራ ስምምነቱ መቋረጡን የሚያሳውቅ ደብዳቤ ከሳዑዲ የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ልማት ሚኒስትር በኩል እስካሁን አልደረሰኝም ብሏል።
ነብዩ ሲራክ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ