1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት  ያፈና ስልት

ረቡዕ፣ ኅዳር 3 2012

መገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት የሳዑዲ አረቢያ ገዢዎች ሰላሳ ሚሊዮን ከሚገመተዉ የሳዑዲ አረቢያ ዜጋ፣ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ የሚጠቀመዉን 10 ሚሊዮን ያክሉን በተለያ መንገድ ይሰልላሉ።

https://p.dw.com/p/3SxCm
Suadi-Arabien Bodyguard von König Salman getötet
ምስል AFP/Saudi Royal Palace/B. al-Jaloud

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት አፈና

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የሚተቹትን ወገኞች ለመከታተልና ለመሰለል የሚረዱ ሁለት የትዊተር ባለሙያዎችን ቀጥሮ በድብቅ ያሠራ እንደነበር ዉስጥ አዋቂዎች አጋለጡ። ዉስጥ አዋቂ ምንጮችን የሚጠቅሱ መገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት የሳዑዲ አረቢያ ገዢዎች ሰላሳ ሚሊዮን ከሚገመተዉ የሳዑዲ አረቢያ ዜጋ፣ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ የሚጠቀመዉን 10 ሚሊዮን ያክሉን በተለያ መንገድ ይሰልላሉ። የነገሥታቱን አገዛዝ ይቃወማሉ፣ ይተቻሉ ወይም ይወቅሳሉ ብለዉ የሚጠረጥሯቸዉን የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ ተጠቃሚዎች ሲችሉ በቀጥታ ካልቻሉ ደግሞ ቤተሰቦቻቸዉን ያጠቃሉ። የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ ተጠቃሚዎችን መልዕክት እየተከታተሉ ለነገሥታቱ የሚያቀርቡት ደግሞ ጠቀም ያለ ገንዘብ የሚከፈላቸዉ ከዚሕ ቀደም ለቲዊተር ኩባንያ ይሰሩ የነበሩ ባለሙያዎች ናቸዉ። ዶቼ ቬለ የእንግሊዝኛዉ ክፍል ያዘጋጀዉን  ዘገባ የፍራንክፈርቱ ወኪላችን እንዳልካቸዉ ፈቃደ እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።

እንዳልካቸዉ ፈቃደ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

: