1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰሞነኛው የሳውዲ ፍተሻ አፈሳ

ሐሙስ፣ የካቲት 12 2012

በሳውዲ መንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች የሚካሄደው የፍትሻና የቤት ሰበራ ዘመቻ ሁሉን የውጭ ዜጎች ያካተተ ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ጨምሮ የጥቂት ሃገራት ዜጎች ላይ ብቻ ያተኮረ ነው መባሉ ስጋት መፍጠሩን  ከጂዳ ነብዩ ሲራክ የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

https://p.dw.com/p/3Y49u
Jeddah in Saudi Arabien
ምስል Getty Images/K. Sahib

«11 ኢትዮጵያውያን ተይዘዋል»

 ካሳለፍናቸው ሳምንታት ወዲህ የሳውድ አረቢያ  መንግሥት ፖሊስ እና የደህንነት አካላት ከፍተኛ የሆነ ፍተሻ በማካሄድ ላይ ናቸው። በሳውዲ መንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች የሚካሄደው የፍትሻና የቤት ሰበራ ዘመቻ ሁሉን የውጭ ዜጎች ያካተተ ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ጨምሮ የጥቂት ሃገራት ዜጎች ላይ ብቻ ያተኮረ ነው መባሉ ስጋት መፍጠሩን  ከጂዳ ነብዩ ሲራክ የላከልን ዘገባ ያስረዳል። ፍተሻውን በሚመለከት ከሚሰራጩ  መረጃዎ ጎን ለጎን ከዚህ ቀደም የተለቀቁ መረጃዎች እንደ አዲስ በማህበርዊ መገናኛው መድረክ በሰፊው መሰራጨታቸው በስላማዊ መንገድ ሰርቶ የሚኖረውን ዜጋም ሳይቀር ስጋት ላይ መጣላቸውንም አመልክቷል።

ነቢዩ ሲራክ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ