የየመን መንግሥት ተቀናቃኝ ኃይሎች መጋጨት
ረቡዕ፣ ጳጉሜን 1 2009ማስታወቂያ
ግንባር ፈጥረው የየመንን መንግሥት ሲወጉ የቆዩት የቀድሞ የየመን ፕሬዝዳንት የአሊ አብዱላ ሳልህ ታማኞች እና የሁቲ አማጽያን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እንደ ቀድሞአቸው አይደሉም። አንዳቸው ሌላኛቸውን በሙስና እና ከበስተጀርባ በማጥቃት ሲወቃቀሱ የከረሞት ሁለቱ ወገኖች መቃቃራቸው ይሰማል። ከዚያም አልፈው ባለፈው ሳምንት ተጋጭተው አንድ የሳህል ከፍተኛ መኮንን እና አማጽያን ተገድለዋል። ይሁን እና ሳልህ በሰጡት መግለጫ በመካከላቸው ምንም ዓይነት ቀውስም ሆነ ግጭት እንደሌለ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የመን ውስጥ በኮሌራ የተያዘው ሰው ቁጥር 612,703 መድረሱ ተነግሯል። ስለ ሳህል ኃይሎች እና ስለ ሁቱ አማጽያን ግጭት እንዲሁም ስለ የመኑ ኮሌራ የሰንአውን ወኪላችንን ግሩም ተክለ ሃይማኖትን ስቱድዮ ከመግባቱ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ግሩም ተክለ ሃይማኖት
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ