1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲዳማዉ ግጭትና ወቀሳዉ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 17 2011

ሲዳማ ዞን የክልል አስተዳደርነት ሥልጣን እንዲኖረዉ በቀረበዉ ጥያቄ መዘዝ የተገደለዉ ሰዉ ቁጥርና የጠፋዉን ንብረት ብዛት በተመለከተ ከክልሉም ሆነ ከዞኑ ባለስልጣናት እስካሁን በይፋ ያስታወቁት ነገር የለም

https://p.dw.com/p/3Mfse
Äthiopien - Pressezusammenfassung der Sidama Liberation Movement (SLM)
ምስል DW/S. Wegayehu

የሲዳማ ግጭትና የሲአን ወቀሳ

 በደቡብ ኢትዮጵያ የሲዳማ ዞንን ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ በሚያብጠዉ ግጭትና ግድያ ለጠፋዉ ሕይወት፤አካልና ንብረት የአካባቢዉ ፖለቲከኞች ወቀሳ ጀምረዋል።ሲዳማ ዞን የክልል አስተዳደርነት ሥልጣን እንዲኖረዉ በቀረበዉ ጥያቄ መዘዝ የተገደለዉ ሰዉ ቁጥርና የጠፋዉን ንብረት ብዛት በተመለከተ ከክልሉም ሆነ ከዞኑ ባለስልጣናት እስካሁን በይፋ ያስታወቁት ነገር የለም።የዓይን ምስክሮችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ግን በግጭቱ በትንሹ 60 ሰዎች ተገድለዋል፤ ብዙ ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት ወድሟል ይላሉ።ተቃዋሚዉ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ለግድያ ግጭቱ «ለተነሳዉ ጥያቄ በሕገ-መንግስቱ መሠረት» መልስ ያልሰጡ ያላቸዉን ወገኖች ተጠያቂ አድርጓል።ንቅናቄዉ ተጠያቂ ያላቸዉን ወገኖች ግን በስም አልጠቀሰም።

 ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋለም ወልደየስ