1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲዳማ ዞን ሕዝበ ውሳኔ በይርጋዓለም

ረቡዕ፣ ኅዳር 10 2012

የሲዳማ ብሄር ራሱን በቻል የራስ ገዝ አስተዳደር ( ክልል ) ለመደራጀት አሊያም የደቡብ ክልል አካል ሆኖ ለመቀጠል በቀረቡ አማራጮች ላይ ከሀዋሳ ብዙም ሳትርቅ በምትገኘው ይርጋለም ከተማም ድምፅ ሲሰጥ ውሏል።

https://p.dw.com/p/3TOUj
Äthiopien: Sidama stimmen über Autonomie ab
ምስል AFP/M. Tewelde

«በሰላማዊ መንገድ ሲከናወን ውሏል»

የሲዳማ ብሄር ራሱን በቻል የራስ ገዝ አስተዳደር ( ክልል ) ለመደራጀት አሊያም የደቡብ ክልል አካል ሆኖ ለመቀጠል በቀረቡ አማራጮች ላይ ድምፅ  ሲሰጥ ውሏል። ዛሬ ከማለዳው አንስቶ የህዝበ ውሳኔ ድምፅ የተሰጠው የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ  በሲዳማ ዞን ወረዳዎች በተዘጋጁ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች ነው። ከኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ አንደሚጠቁመው በህዝበ ውሳኔው በመራጭነት የተመዘገቡ ከሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ድምጻቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Äthiopien: Sidama stimmen über Autonomie ab
ምስል AFP/M. Tewelde

ህዝበ ውሳኔውን በበላይነት እያስፈጸመ በሚገኘው የአገሪቱ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አማካኝነት በየጣቢያዎቹ የተመደቡ አስተባባሪዎችም መራጮች ድምፅ ለመሰጠት ሊከተሏቸው  በሚገባቸው ሂደቶች ዙሪያ ገለጻ በመሰጠት ድጋፍ ሲያደረጉ መመልከቱን ዘግቧል። ይሁንእንጂ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የተዘጋጁ የድምፅ መስጫ ክፍሎች ከተመዝጋቢው ቁጥር ጋር ባለመጣጣማቸው የተነሳ በርካታ መራጮች በረጃጅም መስመሮች ተሰልፈው ድምፅ ለመስጠት ሲጠባበቁ መመልከቱንም በዘገባው ጠቅሷል። በይርጋለም ከተማ በ05 ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ ድምፅ ሲሰጡ ያገኘኋቸው  አቶ ፀጋዬ ዲዳሞ ወጣት ሂሩት ጥላሁን ከሌሊቱ አስራ አንድ ሰዓት ላይ ወደ ምርጫ ጣቢያው በመምጣትና ወረፋ በመያዝ ድምጻቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል። 

የሲዳማ ብሄር ራሱን በቻል የራስ ገዝ አስተዳደር ( ክልል ) ለመደራጀት አሊያም የደቡብ ክልል አካል ሆኖ ለመቀጠል በቀረቡ አማራጮች ላይ ድምፅ  ሲሰጥ ውሏል። ዛሬ ከማለዳው አንስቶ የህዝበ ውሳኔ ድምፅ የተሰጠው የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ  በሲዳማ ዞን ወረዳዎች በተዘጋጁ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች ነው። ከኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ አንደሚጠቁመው በህዝበ ውሳኔው በመራጭነት የተመዘገቡ ከሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ድምጻቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ በይርጋዓለም ከተማና አካባቢው እየተካሄደ የሚገኝውን የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ተዘዋውሮ የተመለከተው የዶቼ ቨለ ( DW ) ዘጋቢ ሸዋንግዛው ወጋየሁ መራጮች ከማለዳው አንስቶ በየምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት ድምፅ በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ዘግቧል። 

Äthiopien: Sidama stimmen über Autonomie ab
ምስል AFP/M. Tewelde

የሲዳማ ብሔር ሕዝበ ውሳኔ የድምፅ አሰጣጥ እየተካሄደ የሚገኘው በክልልና በፌደራል የጸጥታ አባላት በጥብቅ የጸጥታ ጥበቃ ውስጥ ሲሆን በአንዳንድ የግለሰብና የማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይም የክልከላ ገደብ ተደርጓል። በተለይም የሀዋሳ ከተማና የሲዳማ ዞን መስተዳድር የሰላምና  የጸጥታ መምሪያ ኃላፊዎች ከህዝበ ውሳኔው ጋር በተያያዘ ምንም አይነት የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሰልፎችን ማድረግ የተከለከለ መሆኑን በክልሉ መንግሥታዊ  ቴሌቪዥን  « ደቡብ ቲቪ»  በኩል ይፋ አድርገዋል።

ያም ሆኖ የሀዋሳና የይርጋዓለም ከተሞችን ጨምሮ በሲዳማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የድምፅ አሰጣጡ ሂደት አስከአሁን በሰላማዊ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ የዶቼ ቨለ ( DW ) ዘጋቢዎች ከየአካባቢው ያሰባሰቧቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ። በሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ በይርጋዓለም ከተማና አካባቢው እየተካሄደ የሚገኝውን የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ተዘዋውሮ የተመለከተው የዶቼ ቨለ ( DW ) ዘጋቢ ሸዋንግዛው ወጋየሁ መራጮች ከማለዳው አንስቶ በየምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት ድምፅ በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ዘግቧል። 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ