የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ እና ምርጫ ቦርድ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 5 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ብሄር ህዝበ ውሳኔን ለማስፈጸም ያስችለኛል በሚል የጠየቃቸው የሕግና አስተዳደራዊ ማዕቀፎች እስከአሁን ከክልሉ አልቀረበልኝም ሲል አስታውቋል። የሲዳማ ብሄር ህዝበ ውሳኔ ሚስፈጸሚያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት በበኩሉ በቦርዱ የተጠየቀው የህግና አስተዳደራዊ ማዕቀፎች ቢዘገዩም ዝርዝር ህጎች እያዘጋጀ እንደሆነ ገልጿል።በቦርድ ያደረገው የድምፅ ማስጫ ቀን ሽግሽግ ምክንያታዊ በመሆኑ ፓርቲያቸው ተቃውሞ እንደሌለው የገለፁት የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ( ሲአን ) ዋና ጸሀፊ በበኩላቸው ይቅረቡ የተባሉት የህግና አስተዳደራዊ ማዕቀፎች ግን ከአገሪቱ ህገ መንግስታዊ መብቶች ጋር ይቃረናሉ የሚል እምነት የለኝም ብለዋል።ዝርዝሩን የሀዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ልኮልናል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ