1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች ስምምነት

ሰኞ፣ ሐምሌ 29 2011

በሱዳን  ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ወታደራዊው ምክር ቤት እና ሲቪል መንግሥት በሀገሪቱ መመሥረት አለበት በሚል በተቃውሞ ቀጥሎ የሰነበተው ተቃዋሚው ኃይል ትናንት ምሽቱን ታሪካዊ የተባለለት ስምምነት ተፈራርመዋል።

https://p.dw.com/p/3NNHM
Sudan Abkommen - Ahmed Rabie und General Mohamed Hamdan Daglo
ምስል AFP/A. Shazly

«የሽግግር መንግሥት በቅርቡ ይመሠረታል»

 በወታደራዊው ምክር ቤት እና በተቃዋሚው ወገን የተደረሰው ስምምነትም በያዝነው ወር መጨረሻ ገደማ ሱዳን ሲቪሎች የተካተቱበት የሽግግር መንግሥት  ለመመሥረት እንዲትችል ያበቃታል ተብሏል። የሱዳን ወታደራዊ ጀነራሎች የተቆጣጠሩትን ሥልጣን ከሕዝቡ በቀረበው ጥያቄ መሠረት በሲቪል አሥተዳደር ለመተካት ዝግጅኑት ያሳዩት የአፍሪቃ ሕብረት እንዲሁም ጎረቤት ኢትዮጵያ ባካሄዱት ያላሰለ ጥረት እና የሽምግልና ድርድር መሆኑም ይፋ ሆኗል። በወቅቱ የሱዳን ጉዳይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልእክተኛ የሆኑት አምባሳደር መሐሙድ ድሪር በተለይ ለዶይቼ ቬለ «DW» እንደገለፁት በዚህ ስምምነት መሠረት በሱዳን የሽግግር መንግሥት ውስጥ በብዛት የሚካተቱት ሲቪሎች እንጂ መለዮ ለባሾች አይሆኑም። ከዚህ ስምምነት መድረስም ለሱዳን ከአፍሪቃ ሕብረት ጀምሮ በዩናይትድ ስቴትስም ቢሆን የተጣሉባትን ማዕቀቦች እና እገዳዎች ለማስነሳት ዲፕሎማሲያዊ ሚናው ከፍተኛ ነው። ስለስምምነቱ ምንነት በዝርዝር እንዲያስረዱን አምባሳደር መሐሙድ ድሪርን ጠይቀናቸዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ