1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰንደቅ ዓላማችን ጉዳይ

ሰኞ፣ መስከረም 26 2012

በኢትዮጵያ የሰንደቅ አላማ ፖለቲካ በተለይ በህዝቦቿ መካከል ለውዝግብ ፣ ለልዩነትና ለአለመግባባት ምክንያት ሲሆን ይስተዋላል።

https://p.dw.com/p/3QqZ7
Karte Sodo Ethiopia ENG

የሰደቅ ዓላማችን ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ፖለቲካ በተለይ በህዝቦቿ መካከል ለውዝግብ ፣ ለልዩነትና ለአለመግባባት ምክንያት ሲሆን ይስተዋላል። ከአገሪቱ ጥንታዊ ሥነ-መንግስት ምስረታ ጋር ተያይዞ ለረጅም ዓመታት ጥቅም ላይ እንደዋለ የሚነገርለት ልሙጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ አላማ ከሃገሪቱ አልፎ የመላው አፍሪቃ የነጻነትና የአንድነት ተምሳሌት፣ በመላው ዓለምም ጥቁር ነጭን ያሸነፈበት የድል ምልክት ሆኖ ሳለ በሃገር ውስጥ ግን ክብሩን እና የአባቶችን የተጋድሎ አደራ የዘነጋ ነው ሲሉ ብዙዎች ይስማማሉ።  በተለይ ከባለፈው ዓመት ወዲህ በተለያዩ ሁነቶች ላይ በሕገ-መንግስት እውቅና ያለውም ሆነ ልሙጡ፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አርማዎች፣ የክልል ሰንደቅ ዓላማዎች ፣ ዋናውን እየተኩ ሲውለበለቡና አላስፈላጊ ፉክክር ሲታይ ይስተዋላል። ብዙዎች እንደሚሉት  ከሆነ ግን ሕገ-መንግስቱ መሻሻል እንዳለበትና፤ የሰንደቅ ዓላማውም ጉዳይ በዚያው የሚፈታ ይሆናል ነው። 

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ