1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአቶ እስክንድር ጉዳይ ላይ ያወጡት መግለጫ

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 13 2014

በኢትዮጵያ ሁለቱ ዋና ዋና የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ተቆርቋሪ ድርጅቶች ኢሰመኮ እና ኢሰመጉ በእስር ላይ ያሉት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች አያያዝ የታሳሪዎችን መብት በጠበቀ ሁኔታ እንዲሆን ጠየቁ።

https://p.dw.com/p/4261C
Eskinder Nega - Äthiopien Journalist & Menschenrechtsaktivist
ምስል B. Manaye

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአቶ እስክንድር ጉዳይ ላይ ያወጡት መግለጫ

በኢትዮጵያ ሁለቱ ዋና ዋና የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ተቆርቋሪ ድርጅቶች ኢሰመኮ እና ኢሰመጉ በእስር ላይ ያሉት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች አያያዝ የታሳሪዎችን መብት በጠበቀ ሁኔታ እንዲሆን ጠየቁ።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ በሕግ ጥላ ሥር ያሉ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ ምልኩ የመያዝ መብታቸው እንዲከበር ጠይቋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስረኞች ድብደባ ተፈፅሞባቸው መቁሰላቸውን እንዳረጋገጠና የታሳሪዎችን ደህንነት በመጠበቅ ኃላፊነት ዙሪያ ከተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መነጋገሩን አስታውቋል።
ኢሰመጉ በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ የተፈፀመው ድርጊት ተጣርቶ አጥፊዎችም ሆነ የጥበቃ ኃላፊነታቸውን በትክክል ባልተወጡ የማረሚያ ቤቱ ሠራተኞች ላይ አስተማሪ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ