የሰባት ፖለቲካ ፓርቲዎች ሥምምነት
ሰኞ፣ መስከረም 7 2011ማስታወቂያ
ብሔር እና የፖለቲካ አመለካከትን ተኮር ያደረገ ነዉ የተባለዉን ሰሞኑን በኢትዮጵያ የሚታየዉን ግጭት ለመታገል በሃገር ዉስጥ ያሉና ከዉጭ የገቡ በአጠቃላይ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች በኅብረት ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸዉ ተሰማ። ሰባቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደገለፁት በኢትዮጵያ የሚታየዉን ችግር ለመቅረፍ ሁለት ቀናት ከተወያዩ በኋላ ዛሬ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል። የፖለቲካ ፓርቲ ተጠሪዎቹ እንደገለፁት ግጭትና ብጥብጥ የሚፈጥሩትኃይላት በኢትዮጵያ የሚታየዉን የለዉጥ ሂደት ለማደናቀፍ ነዉ።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ