1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሞኑ ኹከትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስሞታዎች

እሑድ፣ ሐምሌ 19 2012

ከሃጫሉ  ግድያ ጋር የሚያገናኛቸው ጉዳይ ያልታወቀ ንጹሀን ዜጎች ላይ ለተፈጸመው ግድያና ለደረሰው የንብረት ውድመት ተገቢው  ፍትህ እንዲሰጥ የሚጠይቁ ጥቂት አይደሉም ።በግድያው ሰበብ የደረሱ  አሰቃቂ የደቦ ግድያዎች ፣ከባድ የንብረት ውድመት የሰዎች መፈናቀል እንዲሁም እስር ብዙ ጥያቄዎችን እያስነሱ ነው ።

https://p.dw.com/p/3ftL1
Äthiopien | Shashemene |  Angriffe und Zerstörungen von Immobilien
ምስል privat

የሰሞኑ ኹከትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስሞታዎች

ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በአዲስ አበባና በኦሮምያ የተለያዩ ከተሞች በጥፋት አድራሾችና  እነርሱን ለመከላከል በተሰማሩ ኃይሎች ልዩ ልዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን በሃገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ዘግበዋል በግድያው ሰበብ የደረሱ  አሰቃቂ የደቦ ግድያዎች ፣ከባድ የንብረት ውድመት የሰዎች መፈናቀል እንዲሁም እስር ብዙ መልስ የሚያሻቸው  ጥያቄዎች እያስነሱ ነው ። መንግሥት በግድያውና በከግድያው በኋላ በተነሱ ሁከቶች ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሰዎች የእስር ይዞታም በሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ተተችቷል።የአንዳንድ እስረኞች ጠበቆችም ደንበኞቻቸው የተያዙባቸው ስፍራዎች ለዘመኑ የጤና ችግር ለኮቪድ 19 የሚያጋልጡ ናቸው ሲሉ  አቤት እያሉ ነው።ፍርድ ቤት የቀረቡ እስረኞችም ይህንኑ ችግር ማንሳታቸው አልቀረም።ሲያዙ መደብደባቸውን የተናገሩም አሉ።ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባለፈው ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ደግሞ መንግሥት የያዛቸው« በርካታ» ያላቸው ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ያሉበትን ቦታ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል።ከሃጫሉ ግድያ በኋላ ደረሱ የተባሉ የመብት ጥሰቶች፣ ምክንያታቸውና ችግሩን በዘላቂነት መከላከያ መፍትሄው የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው። በዚህ ውይይት ላይ የተሳተፉት  አቶ ምስጋናው ሙሉጌታ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ አማካሪ፣  እንዲሁም አቶ ፍስሀ ተክሌ በዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ ናቸው።

ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ።

ኂሩት መለሰ