የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 26 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ለውጥ ለማገዝ ውጭ ያሉ የፖለቲካ ኃይሎች እና አንድ የሆኑት የሃይማኖት አባቶች ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቀረበ። የፓርቲው አመራር አባላት ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ እነዚህ ወገኖችም ሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጡ ወደ ኋላ እንዳይመለስ መጠበቅ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። ቤተ እምነቶች ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ርቀው ሰላም እና ፍቅርን እንዲሰብኩም ጠይቀዋል። በለውጡ ሂደት ትልቁን ሚና የሚጫወቱትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድን እና ባልደረቦቻቸውን ያመሰገኑት የአመራር አባላቱ በአሁኑ ጊዜ መንግሥት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችን በባህላዊ መንገድ ለመፍታት እንዲሞክርም ጥሪ አስተላልፈዋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ