ሰማያዊ ፓርቲ
ረቡዕ፣ ሰኔ 20 2010ማስታወቂያ
ተቃዋሚው የፖለቲካ ድርጅት ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ጥሪ ከተደረገላቸው በውጭ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመሥራት ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀ። የፓርቲው አመራሮች አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጋር በአንድ መድረክ ተገናኝቶ በሀገሪቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎቹን ከመቀበል አንስቶ የሚያስፈልጋቸውን እገዛ በማድረግ እንደሚተባበርም ፓርቲው ገልጿል። በዚሁ መግለጫው ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ የደረሰውን የቦምብ ጥቃት አውግዞ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ